ራእይ/ VISION

KMA ራእይ የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ የወንጌል ተልእኮ ተፈጻሚነት ላይ ያላት ሚና አድጎ ማየት።

ይህም የሚያጠቃልለው (1) ለአንድነት፥ ለመንፈሳዊ ብስለትና ጥራት፥ እንዲሁም ለወንጌል ተልእኮ ታዛዥነት ምሳሌ የሆነ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ክርስትናን መኖርና ማሳየት፥
(2) በዓለም አቀፍ ደረጃ አመራር የሚሰጡ ብቃት ያላቸው መሪዎችን ማሳደግ፥ (3) ወደ ተለያዩ አገሮች መሄድ የሚችሉ ሚሲዮናውያን ማፍራት፥
(4) በሰው፥ በትውልድና በአገር ሁለንተናዊ ግንባታ የተሻለ አስተዋጽኦ ማድረግ።

KMA’s vision is to see the role if the Ethiopian Church math it’s potential and become a significant player in global mission. This includes: (1) to display exemplary Biblical Christianity through unity, spiritual maturity and obedience to the mission of god (2) developing qualified leaders that can give missional leadership in the global stage (3) raising missionaries that can go to all corners of the world (4) making holistic contributions to a person, a generation and nations.








ተልእኮ/ MISSION

ለእግዚአብሔር መንግሥት መስፋፋት ቅድሚያ የሚሰጡ ግለሰቦች፥ አብያተ ክርስቲያናትና መንፈሳዊ ድርጅቶች ጋር በቅንጅት በመሥራት ወንጌልን በቃልና በተግባር ለሕዝቦች ሁሉ ማድረስ።

In partnership with Individuals, Churches and Spiritual organizations  who give priority to the expansion of God’s kingdom; we take the gospel to all peoples of the world by word and deed.



የKMA ዋና ዋና ተግባራት / Key functions of KMA


1. ወንጌልን ለአሕዛብ ሁሉ ለማድረስ በሚደረገው አለም አቀፍ እንቅስቃሴ በሚገባ መሳተፍ፥

በወንጌል ያልተደረሱትን መድረስ፥ ሚሲዮናውያንን መላክና በሚያስፈልጋቸው መደገፍ።

2. ታላቁን ትእዛዝና ታላቁን ተልእኮ አጣምሮ በመታዘዝ የተራቡ፥ የታረዙ፥ የታሠሩ፥ የተገፉና የተቸገሩ ሰዎችን በመርዳትና መንፈሳዊና ሥጋዊ አገልግሎት በመስጠት የምድር ጨውና የዓለም ብርሃን መሆን።

3. የራእይ፥ የአገልግሎት ስልት፥ የአመራርና የተለያዩ ሪሶርሶችን በማሳደግ በዓለም አቀፍ የወንጌል ተልእኮ በብቃት ለመሳተፍ የሚያስችል የአቅም ግንባታ ማድረግ።

4. የወንጌል ተልእኮን አፈጻጸም ለማፋጠን፥ የውጤቱን ጥራት ለማሳደግና የጽድቅ ተጽእኖን ከፍ ለማድረግ ዐቅምን አሰባስበን በቅንጅት መሥራት።

5. ቤተሰብን፥ ልጆችን፥ ወጣቶችንና ታዳጊ መሪዎችን በእግዚአብሔር ቃል እውቀትና በመንፈሳዊ ሕይወት ጥራት እንዲያድጉ መርዳት።

1.To engage in global mission by participating in taking the gospel to all peoples, reaching the unreached, sending and supporting missionaries.
2. To be the salt of the earth and the light of the world by holding the Great Commission and the Great Commandment together and providing holistic ministry to the hungry, the prisoners, the oppressed and the needy
3. To be capable players in global mission, participate in capacity building in the areas of vision, strategy, leadership and resources.

4. Working together in harmony in order to accelerate the fulfillment of the great Commission, increase the quality of our results and make righteous impact.

5. Helping families, children, young people and emerging leaders to grow in the knowledge of God’s Word so that they live the spiritual life of Biblical standards







የሥራው አፈጻጸም / Execution of Plans

KMA የሁላችንም ስለሆነ አፈጻጸሙን የሚመሩ የተለያዩ ግብረ ሃይሎች እንደ አአስፈላጊነታቸው ይቋቋማሉ። ከእነዚህም ግብረ ሃይሎች ዋና ዋናዎቹ የሚከተሉት ናቸው።

  • የጸሎት ግብረ ሃይል
  • የትምህርትና ስልጠና ግብረ ሃይል
  • የልማትና የአስቸኳይ እርዳታ ግብረ ሃይል
  • የአመራር እድገት ግብረ ሃይል
  • የሪሶርስ አሰባሰብና እድገት ግብረ ሃይል
  • የቤተሰብ፥ የልጆችና የወጣቶች ግብረ ሃይል
  • የቴክኖሎጂ እድገትና አጠቃቀም ግብረ ሃይል
  • ዓለም አቀፍ ግንኙነትና ኔትወርክንግ ግብረ ሃይል

Execution of our plans

Since KMA belongs to all of us, we will form different task forces to give leadership as needed. Here are some of the main task forces:

  • Prayer Task Force
  • Education and Training Task Force
  • Development and Emergency Assistance Task Force
  • Leadership Growth Task Force
  • Resources Collection and Development Task Force
  • family, children, and young people task force
  • technological innovation and use task force
  • International Relations and Networking task force.








የKMA አባልነት መስፈርት / KMA Membership Criteria

የሚከተሉትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ግለሰቦች፥ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናት፥ ቤተ እምነቶች፥ መንፈሳዊ ድርጅቶች፥ ፋውንደሽኖችና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ወዳጅ የሆኑ ሁሉ የ KMA አባል መሆን ይችላሉ። የሚከተሉት አሳቦች ለአባልነት መመዘኛ ያገለግላሉ።

• በKMA ዓላማ፥ ራእይና ተልእኮ መስማማት፥

• ለዘላለማዊው ለእግዚአብሔር መንግሥት፥ ለአንዲት የክርስቶስ ቤተ ክርስቲያንና በዘላለማዊ አመለካከት

ለመኖር ቅድሚያ መስጠት፥

• በቅንጅት በመሥራት የሚገኘውን በረከት ለመካፈል ፈቃደኛ መሆን፥

• እርስ በርስ በመዋደድና በመደጋገፍ የቤተ ክርስቲያንን መንፈሳዊና አገልግሎታዊ አቅም ለማሳደግ ፈቃደኛ መሆን፥

• ግለሰቦች፥ አጥቢያ ቤተ ክርስቲያናትና መንፈሳዊ ድርጅቶች የKMAን ተልእኮ በማማከር፥ በብጎ ፈቃደኝነት፥ ሚሲዮናውያንን በመላክና በመቀበል፥ በማቴርያል፥ በገንዘብና በመሳሰሉት ለማገልገል ፈቃደኛ መሆን፥


Individuals, Churches, Churches, Spiritual Organizations, Foundations, and Friends of the Ethiopian church can join the KMA

• With the purpose of KMA, the consensus of vision and mission:

• Prioritizing the eternal kingdom of God, a church of Christ, and living with an eternal perspective:

• A willingness to share in the blessings of good work together in unity.

• A willingness to love and support one another and grow the spiritual service and potential of the church.

• Individuals, local churches and Christian organizations to be willing to send and receive missionaries, to support financially and provide whatever is needed to fulfill the mandate of KMA.







KMA ያስፈለገበት ዋና ዋና ምክንያቶች / 

Key reasons for the need for KMA



አንደኛ፦

ባለፉት አሥርተ ዓመታት የክርስትና ማዕከል ከሰሜን ምዕራባዊ አገሮች ወደ ደቡብ ምስራቃዊ አገሮች ማለትም ወደ “Global South
መዞሩን ብዙ መረጃዎች ያመለክታሉ። ይህም ማለት ኃላፊነትና አመራርም እንዲሁ ይዞራል። ወንጌልን ለምዕራባውያን የማድረስ ተራው የእኛ መሆኑን ያመለክታል። ስለዚህም የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን የሚጠበቅባትን ኃላፊነት ለመወጣት አስፈላጊውን የመንፈሳዊ፥ የሚሲዮናዊና የአመራር ብቃት ግንባታ ማድረግ ይኖርባታል።



First:

Over the past decade, Studies have shown, the center of Christianity has shifted from global North to Global South. That means so does responsibility and leadership need is moving to Global South. This shows us it is our turn to take the gospel to the West. Therefore the Ethiopian church must prepare herself spiritually in order to give missional leadership to fulfill her responsibilities at this time.



ሁለተኛ፦

ለየብቻ ተበታትነን የምንሠራው ሥራ ዐቅሙና ተጽእኖውም ውስን ነው። በመተባበር ከሠራን ግን ከእኛ በላይ የሆነን ሥራ መሥራት፥ ትልቅ ውጤት ማምጣትና ለእግዚአብሔር ክብርና ምስጋና ምክንያት መሆን እንችላለን።



SECOND

The work we do separately has limited potential and influence. But if we work in collaboration, we can do bigger than the sum of our churches and organizations and produce great results and be a cause for God’s glory and praise.


ሦስተኛ፦


ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በማቴ 2414
ወንጌል በዓለም ሁሉ ይሰበካል ብሎ በተናገረው መሰረት ወንጌል ለአሕዛብ ሁሉ ሊደርስ ባለበት በዚህ ጊዜ የኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት በዓለም ዙሪያ ከሚገኙ አብያተ ክርስቲያናትና መንፈሳዊ ድርጅቶች ግንኙነትና ትብብር ማጠናከር ስለሚያስፈልግ KMA
እነዚህን ሁኔታዎች ያመቻቻል ብለን እናምናለን።



THIRD

Our Lord Jesus Christ in Matthew 24:14 told us “this gospel of the kingdom will be preached in the whole world”. We believe KMA can create an ideal environment for the Ethiopian church to work with the Body of Christ globally and other like minded Christian organizations in order to take the gospel to all nations.




አባላት ምን ጥቅም ያገኛሉ / What Benefits Members Get

  • የአባላት ትልቁ ጥቅም የእግዚአብሔርን ዘላለማዊ መንግሥት በማስፋፋት ለእግዚአብሔር ክብር ማምጣት ሲሆን በተጨማሪ የሚከተሉትን ጥቅሞች ያገኛሉ።
    The greatest benefit of members is to bring glory to God by extending His kingdom among all peoples of the earth. Additionally members will receive of the following benefits:
  • የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን በዓለም አቀፍ የወንጌል ተልእኮ አፈጻጸም ያላት ሚና ሲያድግ ማየት
  • አብሮ በመሥራት ያለውን በረከት መካፈል። ለምሳሌ አንዱ ከሌላው መማርና ማደግ፥ ሌላውን ሰው
  • መደገፍና መባረክ፥ የወንጌልን ተልእኮ ማፋጠን
  • ለሚቀጥለው ትውልድ መልካም ምሳሌነትን ማስተላለፍ
  • KMA የሚሰጡትን ትምህርቶች፥ ስልጠናዎች፥ ኮንፍራንሶችና የተለያዩ ማቴርያሎች በነጻ ወይም
  • በቅናሽ ዋጋ ማግኘት
  • በዓለም አቀፍ ኔትወርኮች ውስጥ ግንኙነት የመፍጠርና የመተባበር ጥቅሞች

  • Witnessing firsthand the role of the Ethiopian church grow in the global platform.
  • Sharing the blessing of working together in areas like: learning and growing from one another, supporting and blessing others, accelerating global mission, and being good example for the next generation
  • Receiving free or at a discount trainings and materials produced by KMA.
  • Opportunities to connect and work with like-minded global mission networks

© 2023 Kingdom Mission Alliance All Rights Reserved.​